መጋቢት 15 ቀን 2018 ዓ.ም
በኢትዮጲያ መከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን MNS ማኑፋክቸሪንግ ትሬዲንግ ኤክስፐርት ማናጀር ኪሪስ ሸናይዳ የምርት ውጤት ተዘዋውረው ተመለከቱ።
በመከላከያ ሰራዊት ፋውንዴሽን የአዳማ ጋርመንት ኢንዱስትሪ ዋና ሥራ አሥኪያጅ ኮሎኔል መኮንን በየነ አጠቃላይ የኢንዱስትሪ ሁኔታ ገልፀላቸዋል ።
ከለውጡ ወዲህ የሰራዊቱን ትጥቆችና አልባሳት ጥራት ባለው መልኩ በማምረት ሰራዊቱ ወቅቱ በፈቀደ ደረጃ ከዘመኑ ጋር የዘመነ ትጥቅ መታጠቅ እንዲችል የቆዳና ሽራ ውጤቶችን በተፈለገው ልክ እያመረተ እንደሚገኝ አሥረድተዋል።
የአዳማ ጋርመንት ኢንዱስትሪ ም/ስራ/አስ/ለኦፕሬሽናል ሻለቃ ደሱ ኢንዱስትሪው ለ38 ዓመታት አገልግሎት ሲሰጥ የቆየ መሆኑን ጠቅሰው ለአመታት የማምረት አቅሙ ተገድቦ የቆየ ሲሆን ከለውጡ በኋላ በርካታ ማሽኖችን በማስገባትና በማደስ ኢንዱስትሪውን በማስፋፋት የሰራዊቱን ትጥቆች ከሟሟላት ባለፈ ለሌሎች የፀጥታ ሃይሎች አስፈላጊ ትጥቆችን እያመረተ መሆኑንም ገልፀዋል።



Trackbacks/Pingbacks