በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን አዳማ ጋርመንት ኢንዱስትሪ
ግንቦት 29 ቀን 2018 ዓ.ም
የአድዋ ድል ማይክሮ ፋይናንስ አሁን ያለበትን ደረጃና ቀጣይ በሚከወኑ ተግባራት ዙሪያ ከባለአክሲዮኖች ጋር የምክክር መድረክ አካሂዷል።
ዓላማው በዋናነት ሠራዊቱን ተጠቃሚ ለማድረግ ታስቦ በቅርቡ የተቋቋመው የአድዋ ድል ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም እስካሁን ከ44 ሺህ በላይ አባላትን ማፍራት ችሏል።
አክሲዮን ማህበሩ በቅርቡ ወደ ሥራ ቢገባም በሀገራችን እንደ ጀማሪ የአክሲዮን ተቋም ታሪክ፣ ኪሣራ ሳይገጥመው ከፍተኛ ካፒታል በማስመዝገብ በአጭር ጊዜ ውስጥ ትርፋማነቱን እያረጋገጠ ይገኛል።
አዲስ አበባን ጨምር በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች 15 ቅርንጫፎችን መክፈት የቻለው ማህበሩ ከ2 ቢሊዮን በላይ ከተገዛው አክሲዮን ውስጥ ወደ አንድ ቢሊዮን ብር በመሰብሰብ የካፒታል መጠኑን በፍጥነት እያሳደገ ነው።
ይህ አሃዝና የማህበሩ የአጭር ጊዜ ትርፋማነት ብሎም ፈጣን ዕድገት ፈጥኖ ወደ ባንክ የሚሸጋገርበትና የያዛቸውን የልማት ውጥኖች የሚያሳካ እንደሆነ የዘርፉ ምሁራን ገልፀዋል።
የአድዋ ድል ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አክሲዮን ማህበር በመኮንኖች ክበብ ባካሄደው የባለአክስዮኖች የምክክር መድረክ የማህበሩ የቦርድ ሰብሰቢ ሜጄር ጄኔራል ደረጀ መገርሳ በተገኙበት ቀጣይ አቅጣጫዎችን በማመለከት፣ አክሲዮን ገዝተው ከፍለው ላጠናቀቁ አባላት ዕውቅና ሰጥቷል።
በውይይቱ ክፊያ ያልጨረሱ ባለአክሲዮኖች ፈጥነው ክፊያቸውን እንዲፈፅሙና ማህበሩን እንዲደግፉ ሜጄር ጄኔራል ደረጀ መገርሳ አሳስበዋል።
ማህበሩ ከተቋቋመለት ዓለማ አንፃር ግቡን እየመታ መሆኑን ያነሱት የቦርዱ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ጌታቸው ኃይለማርያም ማህበሩ ከሠራዊቱ አልፎ ለሀገርም ይዞ የሚመጣው ፋይዳ ብዙ በመሆኑ በተባበረ ክንድ ወደ ላቀ ደረጃ ማሸጋገር እንደሚገባ ተናግረዋል።
አሁን ላይ በብድር ፣ በቁጠባና በቢዝነስ ማማከር አገልግሎት እየሰጠ የሚገኘው ፋይናንስ ተቋሙ በ2019 ዓ.ም 21 አዳዲስ ቅርንጫፎችን ለመክፈት፣ ከ800 ሚሊዮን ብር በላይ የብድር አገልግሎት ለመስጠት እንዲሁም ወደ 200 የሚጠጉ አዳዲስ የሥራ ዕድሎችን ለመፍጠር ማቀዱን ሥራ አስፈፃሚው አቶ ዲዳ ሁንዴ ገልፀዋል።
ማህበሩ ባወጣው መመሪያ አክሲዮን ገዝተው ከፍለው ያላጠናቀቁ ባለአክሲዮኖች እስከ ነሐሴ 30/2018 ዓ.ም ከፍለው እንዲያጠናቅቁ ጥሪ አቅርቧል።


