ጥር 14 ቀን 2018 ዓ.ም
የመከላከያ ዋር ኮሌጅ 4ኛ ባች የስትራቴጂክ መደበኛ ተማሪዎች በአዳማ ከተማ የሚገኘውን በኢትዮጲያ መከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን አዳማ ጋርመንት ኢንዱስትሪን ጎብኝተዋል።
በጉብኝት ወቅት ከፍተኛ ጄኔራል መኮንኖች እና የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ሜ/ ጄኔራል ደረጀ መገርሳ የተገኙ ሲሆን፣ የአዳማ ጋርመንት ኢንዱስትሪ ዋና ስራ አስከያጅ ኮ/ል መኮንን በየነ ለጎብኝዎች ስለ ኢንደስትሪው አጠቃላይ ሁኔታ ገለፃ አድርገዋል፡፡
የመከላከያ ዋር ኮሌጅ አዛዥ ሜ/ጄኔራል ቡልቲ ታደሰ የስትራቴጂክ አመራር አንዱ መገለጫው የሀገርን አቅም መረዳትና መተንተን እንዲሁም አማራጭ የፖሊሲ ሀሳቦችን በማመንጨት ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት መቻል በመሆኑ ጉብኝቱ የዚህ አንዱ አካል ነው ብለዋል።
ጉብኝት በተካሄደበት በአዳማ ጋርመንት ኢንዱስትሪ እንደ ተቋም ብዙ ቴክኖሎጂ ነክ የሆኑ ሥራዎች እየተሠሩ ሥለመሆናቸው አመላካች መሆናቸውን የገለፁት ጎብኝዎቹ በኢንደስትሪ ደረጃ እየተተገበሩ ያሉ እነዚህ ምርቶች የሠራዊቱን ብቃትና ዘመናዊነት ከማረጋገጥ አንፃር ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው ተናግረዋል።


