የአድዋ ድል በዓል ምክንያት በማድረግ የተሻለ ስራ አፈፃፀም ለነበራቸው የፋብሪካ ኮካብ የመሰመር ሰራተኞች እና የስታፍ አባላት የደረጃ ዕደገት እና ማበረታቻ ሽልማት ሰጦዋል፡፡
በኢትዮጲያ መከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን አዳማ ጋርመንት እንዱስትሪ
የካቲት 30 ቀን 2018 ዓ.ም
በኢትዮጲያ መከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን አዳማ ጋርመንት እንዱስትሪ “ከአኩሪ ታሪክ ወደ ብሩህ አድማስ” በሚል መሪ ቃል 130ኛውን የአድዋ ድል በዓል በድምቀት አክብረዋል።
በዕለቱ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የአዳማ ጋርመንት እንዱስትሪ ፋብሪካ ዋና ስራ አስኪያጅ ኮ/ል መኮንን በየነ አድዋ በየዓመቱ ሳይሆን በየወሩ ቢዘከር የማይሰለች በደም ቀለም የታተመ ለእኛ የተሰጠ የማይደበዝዝ የጥቁር ህዝቦች ድል ነው ብለዋል።
የአድዋ ድል የታሪክ ፀሃፊዎች ሁሉ የሚመራመሩበት ለተጨቆኑ ህዝቦች የነፃነት ብርሃንን የፈነጠቀ ኢትዮጵያን ከሚያግባቡን ነገሮች ውስጥ ዋነኛው ነው ካሉ በኋላ ኢትዮጵያውያን ከአራቱም አቅጣጫ በመሰባሰብ
በአንድነት ድር ከደር ተገምደው ሀገራቸውን አስቀድመው የራሳቸውን ትጥቅና ስንቅ በመያዝ ብዙ ኪሎሜትሮችን ተጉዘው ታሪክ የሰሩበት የእኛነታችን መገለጫ ነው ሲሉ ገልፀዋል።
የአዳማ ጋርመንት እንዱስትሪ ፋብሪካ ለም/ስራ/አስ/ለኦፕሬሽናል በበኩላቸው የአድዋ ድል የመጀመሪያው የጥቁር ህዝቦች ድል መሆኑን ጠቁመው በሃገራችን ላይ የነጮች ወረራ በተደረገ ጊዜ ህዝቦቿ አንድ ሆነው ፋሽስቱን በመመከት ሀገራችንን ከቀኝ ግዛት ነፃ በማውጣት ነፃ ሃገር አስረክበውናል ብለዋል።
የአሁኑ ትውልድም ከአድዋ የወረሰውን ጀግንነት በመያዝ ሃገራችን የጀመረችውን የልማት ጉዞ ለማደናቀፍ የሚጥሩትን በመታገል የበኩሉን አሥተዋፅኦ መወጣት እንደሚገባው አመላክተዋል።
አሁንም በሀገራችን የመጣ ማንኛውንም ጠላት በፅናት እና በልበ ሙሉነት ለመመከት የሚሠጠንን ሥልጠናም ሆነ ተልዕኮ በድል አድራጊነት መፈፀም ማንነቷ የተረጋገጠች ሀገር ለትውልድ ማሻገር የአድዋ የጀግንነት ታሪክ ለትውልድ ማሥተማር እንደሚገባ ተናግረዋል።







