መጋቢት 7 ቀን 2018 ዓ.ም
አለም አቀፉን የሴቶች ቀን ምክንያት በማድረግ ሴት ስራዊት አባላት እና ሲቪል ሰራቶኞች በፓናል ውይይትና እለቱን በሚዘክሩ የተያዩ ዝግጅቶች በድምቀት ተክብሮ ውሏል።
ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን (ማርች 8 ) “የሴቶች ድምጽ ለእኩልነት እና ለበለጸገች ኢትዮጵያ” በሚል መሪ ቃል ተከብሯል፡፡
ዕለቱ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የአዳማ ጋርመንት እንዱስትሪ ፋብሪካ ዋና ስራ አስኪያጅ ኮ/ል መኮንን በየነ
ከ20ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ ሴቶች ለመብታቸውና ለእኩልነታቸው ያደረጉትን ትግል የምንዘክርበትና የምናስቀጥልበት ቀን መሆኑን በመክፈቻ ንግግራቸው አንስተዋል።
በተላይ ሴቶች ራሳቸውን ማብቃት ለእንዱስትሪ ምርታማነት ለመጨመር ወሳኝ ሆኑን ገልፆዋል፡፡
ሴት ሰራዊት አባላት በበኩላቸው በነበረው የህልውና ዘመቻ ሴቶች ከወንዶች ጋር እኩል ታግለው መሰዋትነት ጭምር ከፍለው ሀገርን ማዳን እንደቻሉት በማስታወስ በቀጣይም የሚሰጣቸውን ማንኛውም ተልዕኮ በድል አድራጊነት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡
በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች ሴቶች የሚደርስባቸውን ፆታዊ ጥቃት በመቃወም ሴቶች በኢኮኖሚያዊ፣ በማህበራዊ እና በፖሊቲካዊ መድረኮች ላይ እኩል ተሳታፊ እንዲሆኑ መስራት ይገባል ብለዋል፡፡
በዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ሂደት ውስጥ የሴቶችን እኩልነትና ተጠቃሚነት ማረጋገጥ አንዱ ማሳያ መሆኑን ጠቁመው ፣ ከለውጡ በኋላም ሴቶችን ወደ አመራርነት ከማምጣት አኳያ በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን ገልጸዋል፡፡
በኢትዮጲያ መከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን አዳማ ጋርመንት እንዱስትሪ የሴቶች ጉዳይ ቡድን መሪ ወ/ሪት መክዳ ሁሴን ቀኑ ለሴቶች እውቅናና ክብር ለመስጠት የሚያስችል ከመሆኑም ባሻገር ሴቶች በማንኛውም ሀገራዊ ጉዳይ ላይ እኩል ተሳትፎ እንዳይኖራቸው እንቅፋት የሚሆኑ ችግሮችን ለመመርመርና መፍትሄ ለመፈለግ የሚያበረታታ መሆኑን አንስተዋል፡፡ ም/መ/አ መሰረት ያይው ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ማርች 8 የሴቶች አካታችነትና ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትን የምናስቀጥልበትና ለሀገር አስተዋፅኦ ያበረከቱ ሴቶችን የምንዘክርበት መሆኑንም አንስተዋል፡፡



