በሜጀር ጄነራል በርሄ ገ/መድህን የተመራ የልዑካን ቡድን የአዳማ ጋርመንት ኢንዱስትሪን ጎበኘ
በመከላከያ ሎጀስቲክስ ዋና መምሪያ የሜይንቴናንስ መመሪያ ኃላፊ በሜጀር ጄነራል በርሄ ገ/መድህን የተመራ ከፍተኛ ጄነራል መኮንኖች በመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን ስር የሚገኘውን የአዳማ ጋርመንት ኢንዱስትሪን የሥራ እንቅስቃሴ ጎብኝቷል።
አጠቃላይ የኢንዱስትሪውን የሥራ እንቅስቃሴ በተመለከተ ማብራሪያና ገለጻ የተደረገ ሲሆን፣ የፋውንዴሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሜጀር ጄነራል ደረጃ መገርሳ የኢንዱስትሪውን ሁለንተናዊ የሥራ ጉዞና እቅዶችን አስመልክተው ለጎብኚዎቹ ገለጻ አድርገዋል።
በተጨማሪም የአዳማ ጋርመንት ኢንዱስትሪ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሻለቃ ደሱ አብዲሳ በፋብሪካው ውስጥ ያለውን ተጨባጭ የሥራ እንቅስቃሴ፣ የማምረት አቅም እና ተያያዥ የስራ ሂደቶችን በተመለከተ ለልዑካን ቡድኑ ሰፊ ማብራሪያና ገለጻ ሰጥተዋል።
የጉብኝቱ ተሳታፊዎችም ኢንዱስትሪው እያከናወነ ባለው የስራ እንቅስቃሴ ላይ ያላቸውን አድናቆት ገልጸው፣ በቀጣይ ስራዎችን ይበልጥ ለማጠናከር በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ መክረዋል።


