የአዳማ ጋርመንት ኢንዱስትሪ ህዳር 11 ቀን 2019 ዓ.ም
የአዳማ ጋርመንት ኢንዱስትሪ የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ዳይሬክቶሬት የነጭ ሪቫን ቀንን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ35ኛ፣ በሀገር አቀፍ ደረጃ ደግሞ ለ21ኛ ጊዜ በድምቀት አክብሯል። ዕለቱ የተከበረው “ለተጎጂዎች ፍትህ፣ ለወንጀለኞች ተጠያቂነት፣ ለሴቶችና ታዳጊዎች ደህንነት“ በሚል መሪ ቃል ነው።
በኢንዱስትሪው ዋና መስሪያ ቤት አዳራሽ የተካሄደውን የዕለቱን መድረክ የመሩት ኮሎኔል ብርቱካን ተሾመ ናቸው። ኮሎኔል ብርቱካን በንግግራቸው፣ ከመሪ ቃሉ እንደምንረዳው ሴቶችንና ህፃናትን ከጥቃት በመጠበቅ ተገቢውን ክብርና ከለላ መስጠት ከተቻለ፣ ሴቶች ከወንዶች እኩል የሀገራችንን የሰላም፣ የልማትና የዴሞክራሲ ህልሞች ለማሳካት የላቀ ሚና እንደሚጫወቱ አስገንዝበዋል።
በመድረኩ የተሳተፉ የኢንዱስትሪው አመራሮችና አባላትም ከመሪ ሀሳቡና ከግል ተሞክሯቸው በመነሳት ሴቶችን የሚያበረታቱ ገንቢ አስተያየቶችን አንስተዋል። ውይይቱም ተሳታፊዎች በቀጣይ ከሴት እህቶቻቸው ጎን በመቆም ማንኛውንም ዓይነት ጾታዊ ጥቃት ለመከላከል በጋራ ቃል በመግባት ተጠናቋል


