በባህልና ስፖርት ሚኒስቴር አዘጋጅነት በመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን አዳማ ጋርመንት እንዱስትሪ እየተካሄደ ያለው የታዳጊ ወጣቶች ስፖርት ስልጠና ምዘና ውድድር በስፖርታዊ ጨዋነት እየተካሄደ ይገኛል።
ከ13 እስከ 15 ዓመት በታች የታዳጊ ወጣቶች ስፖርት ስልጠና ምዘና ውድድር አካል የሆነው ውሃ ዋና ስፖርት ውድድር የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን አዳማ ጋርመንት እንዱስትሪ
ሲካሄድ ውሏል። የምዘና ውድድሩ በነፃ ቀዘፋ፣ ጀርባ ቀዘፋ፣ ቢራቢሮ ቀዘፋ፣ ደረት ቀዘፋ እና ጀርባ ቀዘፋ የማጣሪያ እና የፍፃሜ ውድድሮች በሁለቱም ፆታ ተካሄዷል።

