በባህልና ስፖርት ሚኒስቴር አዘጋጅነት በመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን አዳማ ጋርመንት እንዱስትሪ የታዳጊዎች ልማት ለኢትዮጵያ ከፍታ ” በሚል መሪ ሃሳብ ሲካሄድ የነበረው ሀገር አቀፍ ከ13 እስከ 15 ዓመት በታች የታዳጊ ወጣቶች ስፖርት ስልጠና ምዘና ውድድር በመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን አዳማ ጋርመንት እንዱስትሪ የውኃ ዋና ስፖርት ፍፃሜውን አግኝተዋል።
የውኃ ዋና ስፖርት ዛሬ ሲጠናቀቅ፤ አማራ ክልል 25 ወርቅ ሜዳሊያዎችን በማግኘት ውድድሩን በበላይነት አጠናቋል።በማጠቃለያ መርሃ ግብሩ ለይ የተገኙት የመከላከያ ሰራዊት ፋውንዴሽን የአዳማ ጋርመንት እንዱስትሪ ዋና ስራ አስኪያጅ ኮ/ል መኮነን በየነ ከ1-3 ደረጃ ለወጡ ስፖርተኞች ሽልማት ሰጠዋል::


