መከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን አዳማ ጋርመንት እንዱስትሪ የካቲት 20 ቀን 2018 ዓ.ም
130ኛውን የአድዋ ድል በዓል መታሰቢያን አስመልክቶ በመከላከያ ሠራዊት ፋዉንዴሽን አዘጋጅነት ሲካሄድ የቆየው 3ኛ ዙር አድዋ ድል ካፕ ስፖርታዊ ውድድር ተጠናቀቀ።
በዕለቱ በክብር እንግድነት የተገኙት የመከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሀመድ ለ130ኛው የአድዋ ድል በዓል እንኳን አደረሳችሁ ብለው ውትድርና የብዙ ቴክኖሎጂና ዕውቀት ማፍሪያ ከመሆኑም ባሻገር በስፖርቱ ዘርፍም ሀገር ያስጠሩ አንጋፋ ስፖርተኞች መፍለቂያ መሆኑን ገልፀዋል።
ውትድርና እና ስፖርት የማይነጣጠሉ ናቸውና የሠራዊቱን ስነ-ልቦናዊና አካላዊ ብቃትን በማጎልበት ረገድ ሚናው ከፍ ያለ ከመሆኑም በላይ የሠራዊቱን ፍቅር እና አንድነትን ያጠናክራል ብለዋል ሚንስትሯ።
ለሀገር ተተኪ ስፖርተኞችን ለማፍራት መከላከያ በስፖርቱ ዘርፍ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው ያሉት ኢንጂነር አይሻ መሀመድ የአድዋን በዓል ስናከብር ለሀገር ሠላም ፣አንድነትና ዕደገት በጋራ በመቆም መሆን እንደሚገባውም ጠቁመዋል።
ፋውንዴሽኑ የሠራዊቱን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ተልዕኮውን በብቃት እየተወጣ መሆኑን የገለፁት የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሜጄር ጄኔራል ደረጄ መገርሳ በስፖርታዊ ውድድሩ በክፍሎች መካከል አንድነትና መደጋገፍ የታየበትና የአድዋ ጀግኖችን የዘከረ ሥለመሆኑ ተናግረዋል።
በእግር ኳስ ፍፃሜ የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን ሎጂስቲክስ ዋና መምሪያ 4 ለ 1 በሆነ ውጤት የረታ ሲሆን በውድድሩ አሸናፊ ለሆኑ የዋንጫ እና የሜዳለያ ሽልማት ለባለድርሻ አካላት እና ውድድሩን ላስተባበሩ ደግሞ የምስጋና እና የዕውቅና ሰርተ-ፊኬት ተበርክቶላቸዋል።






