የካቲት 25 ቀን 2018 ዓ.ም
በመከላከያ ትምህርትና ስልጣና ዋና መምሪያ ሎጀስቲክስ ኮሌጅ አመራሮችና ተማሪዎች በኢትዮጲያ መከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን አዳማ ጋርመንት እንዱስትሪ እየተካሄደ ያለውን አጠቃላይ የፋብሪካ የማምረት ስራዎች ተመልክተዋል።
ለጎብኝዎቹ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያሥተላለፉት የአዳማ ጋርመንት እንዱስትሪ ፋብሪካ ዋና ስራ አስኪያጅ ኮ/ል መኮንን በየነ ናችው፡፡
ሎጀስቲክስ የሠራዊቱ የጀርባ አጥንት ነው ያሉት የአዳማ ጋርመንት እንዱስትሪ ፋብሪካ ለም/ስራ/አስ/ለኦፕሬሽናል ሻለቃ ደሱ አብዲሳ፣ የሎጀስቲክስ ሙያተኛ የሠራዊቱን ሀብት በቁጠባ፣ በታማኝነት እና በስትራቴጂያዊ እውቀት ማስተዳደር የሚችል የሠራዊቱ የደም ስር መሆኑንም አብራርተዋል።
መቶ አለቃ ሰማው አራጌ እና የቡድኑ አባላት በጉብኝቱ መደሰታቸውን ገልፀዋል። በአዲስ ማሽን አዳዲስ ምርቶች በፍጥነትና በጥራት መመረታቸውን፣ ሠራዊቱ ሠላም ከማረጋገጥ በዘለለ በቴክኖሎጂው ዘርፍ ወደፊት መራመዱ፣ መከለከያ ግዙፍነቱን አሥጠብቆ መቀጠሉን የሚያረጋግጡ እውነታዎችን ተመልከተናል ብለዋል።



