በኢትዮጲያ መከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን አዳማ ጋርመንት እንዱስትሪ
መጋቢት 8 ቀን 2018 ዓ.ም
በኢትዮጲያ መከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን አዳማ ጋርመንት እንዱስትሪ የመቆያ ጊዜያቸውን ለሸፈኑና ውጤታማ የስራ አፈፃፀም ላስመዘገቡ የአዳማ ጋርመንት እንዱስትሪ አባላት የማዕረግ የማልበስ ስነ-ስርአት አካሂዷል።
በስነ ስርዓቱ ላይ ተገኝተው ለተሿሚዎች ማዕረግ በማልበስ የስራ መመሪያ የሰጡት የአዳማ ጋርመንት እንዱስትሪ ዋና ስራ አስኪያጅ ኮ/ል መኮንን በየነ የማዕረግ ሹመት የሚሰጠው የመቆያ ጊዜያቸውን ሸፍነው በስራ አፈፃፀማቸው ብልጫ ላስመዘቡና በቀጣይም ተጨማሪ ሃላፊነት ለመቀበል ዝግጁ ለሆኑ ጀግኖች ነው ብለዋል።
ዛሬ ይህንን ዕድል ያገኛችሁ ተሿሚዎች አሁን ካስመዘገባችሁት በላይ የላቀ የስራ ውጤት እንደሚጠበቅባችሁ በማመን ሁሌም ጠንክራችሁ መስራት ይገባችኋል ሲሉ አሳስበዋል።
የአዳማ ጋርመንት እንዱስትሪ ም/ስ/አስኪያጅ ለሃብት አስተዳደር ሌ/ኮ ጴጥሮስ ታምራት የማዕረግ እድገት ያገኙ እንዱስትሪ አባላት የመቆያ ጊዜያቸውን የሸፈኑ፣በስራ አፈፃፀማቸው እና በስነ-ምግባራቸው የተመሰገኑ ስለመሆናቸው ያስረዱ ሲሆን የተቋሙን የመመልመያ መስፈርቶች ሁሉ አሟልተው ለሹመት የቀረቡ መሆናቸውን ተናግረዋል።


