መከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን አዳማ ጋርመንት ኢንዱስትሪ እርሻ ልማት የግብርና ስራ እንቅስቃሴ በጥሩ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ተገለፀ
የእርሻ ልማት በፍራፍሬ ማለትም ሙዝ፣ ፓፓያ፣ አቨካዶ፣ እና በአታክልት ልማት ሽንኩርት፣ ቲማቲም በጥሩ ሁኔታ እየለሙ መሆኑን የአዳማ ጋርመንት እንዱስትሪ ም/ስ/አስኪያጅ ለሃብት አስተዳደር ሌ/ኮ ጴጥሮስ ታምራት ገልፀዋል፡፡
እርሻ ልማቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ የግብርና ምርቶችን ጥራት መጠን በመጨመር ሳይቆራረጥ ህብረተሰቡ ከምርቱ ተጠቃሚ እንዲሆን በትኩረት እየሰራ መሆኑን የተናገሩት ም/መ/አ መሰረት ያይው የግብርና ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለሲቪል ሰረተኞች እና ለሰራዊት አባላት የማቅረብ ስራው ይቀጥላል ብላለች፡፡






