ሜጀር ጄነራል ደረጀ መገርሳ በአዳማ ጋርመንት ኢንዱስትሪ ያለውን የሥራ እንቅስቃሴ ጎበኙ
የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ ክቡር ሜጀር ጄነራል ደረጀ መገርሳ በአዳማ ጋርመንት ኢንዱስትሪ በመገኘት ተቋሙ ያለበትን አጠቃላይ የሥራ እንቅስቃሴ ተመለከቱ።
በጉብኝቱ ወቅት የኢንዱስትሪው ዋና ሥራ አስኪያጅ ሻለቃ ደሱ አብዲሳ ለዋና ሥራ አስፈፃሚውና ለልዑካን ቡድኑ ሰፊ ገለፃ አድርገዋል። ሻለቃ ደሱ በገለፃቸው፤ ኢንዱስትሪው ለሠራዊቱና ለሲቪል ማህበረሰቡ ጥራቱን የጠበቀ አልባሳት በተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብ እያከናወነ ያለው ን ተግባርና ተቋሙን በቴክኖሎጂ ለማዘመን እየተደረገ ያለውን ጥረት አብራርተዋል።
በዚሁ መርሐ-ግብር ላይ የተገኙት የአዳማ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ የሥራ አስፈፃሚ አቶ
ፅጌ ጌታቸው ከሜጀር ጄነራል ደረጀ መገርሳ ጋር በመሆን በኢንዱስትሪው ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ የምርት ክፍሎችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል። በጉብኝቱም በአዳማ ጋርመንት እና በአዳማ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ መካከል ያለውን የሥራ ትስስር ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ መክረዋል።
ሜጀር ጄነራል ደረጀ መገርሳ በበኩላቸው፤ ኢንዱስትሪው የ ሠራዊቱን የአልባሳት ፍላጎት በሀገር ውስጥ ምርት በመሸፈን ረገድ እያበረከተ ያለው አስተዋጽኦ የሚደነቅ መሆኑን ገልጸዋል።


